ብሎክቼይን አዲሱ ኢንተርኔት

By Geleta Gammo

 

ብሎክቼይን ማለት በመሰረቱ ያልተማከለ የመረጃ መዝገብ ነው። በዚህ የመረጃ መዝገብ ላይ የሚመዘገቡ ነገሮች ሁሉ
1፣ ያልተማከለ ነው። ማለት፣ አንድ መረጃ በብሎክቼይን ላይ ሲመዘገብ የመረጃው ቅጂ ከብሎክቼይኑ ጋር በተያያዙ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኮምፑተሮች ሁሉ ላይ ይቀመጣል። ይህ ማለት መረጃው ሊጠፋ አይችልም።

ምሳሌ1፣ በስሜ የተመዘገበ የቤት ካርታ ቢኖረኝና ይህንን ብሎክቼይን ላይ ባስመዘግብ ያ የኔን ስም የያዘ ካርታ ተባዝቶ በመላው ዓለም ባሉ ኮምፑተሮች ይቀመጣል። የኔ ኮሙፑተር ቢሰረቅ ካርታው በኔ ስም እስካለ ድረስ ምንም ለውጥ አያመጣም።

ምሳሌ 2፣ አንድ ሰው የህክምና ታሪክ መዝገብ አለው ብንል ይህ መዝገብ በብሎክቼይን ላይ ከተቀመጠ ሁሌም አዲስ ነገር ሲመጣ እየተጨመረበት ይኖራል። ወደ አዲስ ዶክቶር ጋ ሰውዬው ሲሄድ የመዝገብ ቁጥሩን ቁልፍ ለዶክቶሩ ሲሰጠው የታማሚውን የጤና ታሪክ ዶክቶሩ አይቶ የበለጠ ይረዳል።

ምሳሌ3፣ አንድ ሰው ማንነቱን ለማሳወቅ ራሱን ሊያሳውቁ ከሚችሉት ነገሮች ጋር አንድ ጊዜ ራሱን ብሎክቼይን ላይ መመዝገብ ብቻ ነው። ለምሳሌ ፎቶውን የጣት አሻራውን ቢያስቀምጥና ከዚህ መታወቂያው ጋር የቤት ካርታውን ወይም የህክምና መዝገቡን የባምክ ቁጥሩን ቢያያይዝ፣ ሌላ መታወቂያ አያስፈልገውም። የትም ዓለም ቢሄድ ፓስፖርት አያስፈገውም። ማንነቱን ከብሎክ ቼይን ላይ ማሳየት ይችላል። ማሳየት ለሚፈልገው ብቻ ያሳያል።

2፣ መረጃው ተመስርጠው (encrypted) ሆነው ይመዘገባሉ። ይህ ማለት ቁልፉን ከያዘው በስተቀር ማንም ሊያየው አይችለም። ቁልፎቹ ሁለት ናቸው። አንደኛው የባሌበቱ ቁልፍ ሲሆን ሌላው ሌላ ሰው እንዲያይ የሚሰጥ ቁልፍ ነው። ይህ ለሌላ የሚሰጠው በተቀባዩ መታወቂያ ቁልፍ ስለሚመዘገብ የተሰጠው ሰውየ ብቻ ነው ሊያይ የሚችለው። ለሌላ አሳልፎ መስጠት አይችልም። ያንን እንዲያደርግ ፈቃድ ካልተሰጠው በስተቀር። ባለቤቱ በፈለገው ጊዜ ያንን ለሰው የተሰጠ ቁልፍ መሰረዝ ይችላል።

ምስሌ 1፣ የተገለጸው የቤት ካርታ ሙሉ በሙሉ ለሁሉም እንዲታይ፣ የተወሰነው መረጃ ብቻ እንዲታይ፣ ለተወሰነ ሰው ብቻ እንዲታይ ማድረግ ይቻላል። ለምሳሌ የባለቤቱ ስም እንዳይታይና የመሬቱ ስፋት ብቻ ለህዝብ እንዲታይ ማድረግ ይቻላል። ፍርድ ቤት ሲቀርብ ዳኛውና ፖሊስ ብቻ ስሙ ምን እንደሚል ማሳየት ይቻላል።

ምሳሌ3፣ የህክምና መረጃው ለዶር ብቻ እንዲታይ ማድረግ ይቻላል። ዶሩ ህክምናውን ሲጨርስ ለሱ የተዘጋጀው ቁልፍ ከተሰረዘ ዶሩ ተመልሶ መግባት አይችለም።
ነገር ግን ስም ሳይታይ የበሽታው ዓይነት፣ የተወሰደው መድሃኒት፣ ለመዳን የወሰደበት ጊዜ የመሳሰሉት ለሁሉም ዶክቶሮች ወይም ተመራማሪዎች ስም ሳይኖር እንዲታይ ማድረግ ይቻላል። ያ ማለት ተመራማሪዎች ስንተ በዚህ በሽታ ታማሚ እንዳለና የትኛው መድሃኒት እንደሚሰራ ማወቅ ይችላሉ። ይህ ለምርምር በጣም ጠቃሚ ነው። እስከ ዛሬ ያሉ የህክምና ምርምሮችን አስቸጋሪ የሚያደርገው እንዲህ ዓይነት መረጃ አለመገኘት ነው።

ምሳሌ3፣ የጣት አሻራውን ከብሎክ ቼይን ጋር በማመሳከር ማንነቱንና ከየት እንደመጣ እንዲታወቅ አድርጎ ማስመዝገብ ይችላል። ሌላውን መረጃ ተጨማሪ ቁልፍ አድርጎበት። ያ ማለት ሰውዬው የትም አገር ሄዶ ራሱን ቢስት ቢያንስ ማን እንደሆነ ከየት እንደመጣ ወዲያው ይታወቃል። የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ቢያስቀምጥና ሁለት ሶስት እንዲህ ዓይነት ሰዎችን አብረው ከፈረሙ ሌላው መረጃው ሁሉ እንዲታይ ማድረግ ይችላል።
ቢሞት አምስት የሚያምናቸው ሰዎች ከፈረሙበት በሱ ስም የተመዘገቡ ንብረቶች ለማዛወር እንዲቻል ማድረግ ይቻላል፡
የመክፈቻ ቁልፉ ቢጠፋበት ማንነቱን የሚገልጹ ቀድሞ የመረጣቸው አምስት ሰዎች እንዲፈርሙ ባምድረግ ማንነቱን ማሳወቅ ይችላል። ያ ማለት ማንም ሌላውን አስመስኦ ምንም ማድረግ አይችልም። (identity theft) አይኖርም።

3፣ በዚህ የመረጃ መዝገብ ላይ የተመዘገበ ነገር መሰረዝ ወይም መቀየር አይቻልም። መረጃው ብሎክቼይን የተባለበትም ምክንያት ለዚህ ነው። መረጃው በጥቅል ጥቅል ተደርጎ ርስበርሱ በተመዘገበበት ጊዜ ቅደም ተከተል ይቀመጣል። ይህ ቅደም ተከተል አይዛነፍም። የመጀመሪያውና የሚቀጥለው መረጃ በጊዜ ማኅተም (time stamp) የተቆራኙ በመሆናቸው በመሃከላቸው አዲስ ነገር ማስገባት አይቻልም።

ምሳሌ1፣ የቤት ካርታው አንዴ ከተመዘገበ ባለቤቱ እስካልፈረመ ድረስ ለዘላለም እዛው ይኖራል። ነገርግን ቤቱ ቢሸጥ ካርታው መዝገቡ ላይ ካርታው ወደየት እንደሄደ ተመዝግቦ ወደ አዲሱ ባለቤት መዝገብ ይገባል። አዲሱ ባለቤት መዝገብ ላይም ካርታው ከየት፣ መቼ እንደመጣ ይመዘገባል። ይህ የተመዘገበው ነገርም ለዘላለም አይጠፋም።

ምሳሌ2፣ ይህንኑ ካርታ ሌላ ዋጋ ያለው ነገር ነው ብንል፣ ለምሳሌ መኪና፣ አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብር ነው ብንል ፣ መኪናውም ሆነ አልማዙ፣ ወርቁም ሆነ ብሩ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሄደና ለምን እንደሄደ (በሽያጭ ይሁን በስጦታ) ተመዝግቦ ለዘላለም ይቀመጣል። ማንም ሰው ሊሰርዘው ሊደልዘው አይችልም። አንድ ሰው ራሱ ኮምፑተር ላይ ያለውን ብሎክቼይን ውስጥ ያለውን መረጃ ወደ ኋላ ሄዶ ቢቀይር ምንም ጥቅም የለውም። ምክንያቱም የተቀየረበትን ጊዜ ሌሎች ኮፑተሮች ከራስቸው መረጃ ጋር ስለሚያመሳክሩ አይቀበሉትም።

ይህ ማለት ሙስናና ስርቆት በፍጹም የማይቻል ይሆናል ማለት ነው።

4፣ ብሎክቸይን ሶስተኛ ምስክር አይፈልግ።
አሁ ባለበት ሁኔታ ማንኛውምንም ንብረት ለማስተላለፍ ወይ የውልና መረጃ መሄድ ወይም ምስክሮችን ማቆም ያስፈልጋል። ወይ ፍርድ ቤት መሄድ ያስፈጋል። ይህ ደግሞ ጊዜና ገንዘብ ይፈጃል።

ምሳሌ፣ ቤቴን ወይም መኪናዬን መሸጥ ብፈልግ፣ ሶስተኛ ምስክር ወይም መገናኛ መሄድ አያስፈልገኝም። ሰውዬውንም ማግኘት አያስፈልገኝም። ገዢና ሻጭ ከተስማሙ የብሎክቼይን ውል ይፈራረማሉ። ይህ ውል በብሎክ ቼይን ብልጥ ውል (smart contract) በመባል ይታወቃል።
በመሰረቱ ይህ ውል የኮምፑተር ፕሮግራም ነው። ማንኛውም የኮምፑተር ፕሮግራም በመሰረቱ ትዕዛዝ ነው። ሁሉም ፕሮግራሞች ይህ ሲደረግ ይህንን አድርግ የሚል ትዕዛዞች ናቸው።

ይህ ወደ ውል ሲቀየር ከገዢ አካውንት አንድ መቶ ሺህ ብር ወደ ሻጭ አካውንት ሲገባ የካርታውን ወይም የመኪናውን ስም ወደ ገዢ አዙር ተብሎ የሚጻፍ ውል ነው። በሶስት ቀን ውስጥ ገንዘቡ ካልገባ ውሉ ይሰረዝ የሚልም ሊጨመርበት ይችላል። መያዣ አንድ ሺህ ብር ሲገባ ውሉ የሶስት ቀን ገደቡን እንዲያከብር፣ መያዣ ካልገባ ለ 1 ሰዓት ብቻ እንዲጠብቅም ማዘዝ ይቻላል። የተለያየ ዓይነት ትዕዛዝ መስጠት ይቻላል።

ይህንን ውል ሁለቱም በብሎክቼይን ላይ የግል ቁልፋቸውን በማሳየት ይፈርማሉ። ይህ ውል ከተፈረመ በኋላ በሁለቱም ስምምነት ካልሆነ የትኛውም ወገን በራሱ ሊቀይረው አይችልም። መሰረዝም ማስተካክለም አይቻልም። በዚህ ውል መሰረትም፣ ቤቱም ሆነ መኪናው በውሉ ጊዜ ለሌላ ሰው እንዳይተላለፉ መቆለፍም ይቻላል።
ገዢው የተዋዋሉትን ገንዘብ መጠን በሻጩ አካውንት ሲያስገባ ወዲያውኑ የቤቱ ካርታም ሆነ የመኪና ሊብሬው ወደ ገዢው ይተላለፋል።

ለምሳሌ የመኪናው ቁልፍ ወይም የቤቱ ቤት ቁልፍ በእጅ አሻራ የሚከፈት ቢሆን መኪናው ከዛ በኋላ በቀድሞው ባለቤቱ አሻራ አይከፈትም ማለት ነው። መኪናው አልነሳም ሊልም ይችላል።
ዛሬ ስልኮች ሳይቀሩ በአሻራ መክፈትና መዝጋት በሚቻልበት ጊዜ ይህንን ማድረግ በጣም ቀላል ነው።

5፣ ብሎክቼይንን በመጠቀም የምርጫ ድምጽ መስጠት ይቻላል። በብሎክ ቼይን የተደረገ ምርጫን መስረቅ አይቻልም። ይህ ማለት ዲሞክራሲ….

6፣ የብሎክ ቼይንን ጥቅም ላይ የሚያውል ድርጅት መዝገቡ ሊሰረቅበት አይችልም፣ ጉልበተኛ ሊዘጋው አይችልም፣ ሌቦች፣ ሙሰኞች ሊበሉት አይችሉም…

ዘላለማዊ ይሆናል ማለት ነው።