«የራእየ ማርያም ትርጉም ችግር» (ጥናታዊ ጽሑፍ)-ኣደባባይ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በግራ ዘመም እና መሠረተ-ጎሳ በሆኑ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰቦች ዘንድ በጠላትነት እንደምትፈረጅ የአደባባይ ምሥጢር ነው። በዚህ ረገድ የሕወሐት የ40 ዓመት ፖለቲካ እና በኦነግ እና ከዚያም በኋላ በተነሡ የኦሮሞ ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ ያለው አመለካከት ተጠቃሽ ነው። እነዚህ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ቤተ ክርስቲያኒቱን በጠላትነት የፈረጁበትን ዝርዝር ጉዳይ ለጊዜው ብናቆየው እና በኦሮሞ ልሒቃን አካባቢ የሚጠቀሰውን አንድ መጽሐፍ…