የኢትዮ ሱዳን ድንበርን ለማጣራት ያደረግኩት ድካምና ውጤት

 By Muluken Tesfaw የኢትዮ ሱዳን ድንበርን ለማጣራት ያደረግኩት ድካምና ውጤት ክፍል ፩ የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ አደርኩ፡፡ እራት ላይ ‹ትእቢት› የሚባል ምግብ በልቼ ተሰቃይቻለሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ናይል ሆቴል ከአንድ የቀዬ ወዳጄ ጋር ሒደን ራት ስናዝዝ ‹የቤቱ ምርጥ ዛሬ ምንድን ነው?›› አልናት አስተናጋጇን፡፡ ‹‹ትእቢት ይምጣላችሁ›› አለችን፡፡ በስሙ እየተገረምን ምግቡ ምን ዓይነት ይሆን ይሆን?…